ለሀገራችን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ስኬታማነት ሁሉም የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት – ኃይለየሱስ ታዬ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለሀገራችን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ስኬታማነት ሁሉም የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት የህገ መንግስትና ፌደራልዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ገለጹ።
ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለዋናው እና ለቅርንጫፍ ጣቢያዎች አመራሮችና ጋዜጠኞች የአሠልጣኞች ስልጠና አካል የሆነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በሀዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ ላይ ተካሂዷል።
በዚህ መርሀ-ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱስ፤ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ጥቅሙ የትየለሌ ስለሆነ ሌሎችም ተመሣሣይ ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘላለም ገነሞ በበኩላቸው፤ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ከህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ጋር በጋራ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው የጥላና የፍራፍሬ ችግኞች በታቦር ተራራ ላይ መትከል መቻሉን ጠቁመዋል።
አክለውም ማዕከሉ ከደሬቴድ ጋር በዚህና በሌሎች የአስተምህሮ መርሀ-ግብሮች እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሀ-ግብሩ የማዕከሉ፣ የደሬቴድ እና የቅርንጫፍ ጣቢያ አመራሮችና ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ ታሪኳ በቀለ

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ