የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሀላባ ዞን የመስክ ምልከታ ማድረግ ጀመረ
በምክር ቤቱ የፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሰቢ አቶ ታመነ ገብሬ የመሩት የቅኝት ቡድን በሀላባ ከቶቲ ኡሎ ወረዳ የተለያዩ ስራዎችን እየተመለከቱ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው በአቶቲ ኡሉ ወረዳ የቆልቻ 2 ድልድይ፣ በዌራ ዲጆ ወረዳ የሌጋሞ ድልድይ፣ እንዲሁም ቆቦ ማዞሪያ-ቆቦ-አሻሻሬ የገጠር መንገድ የግንባታ ሂደትን ተመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይ ቀናትም በክልሉ የተለያዩ ዞኖች በመንግስት እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተዟዙሮ ይመለከታል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ