ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የህዝብና የመንግስት አገልግሎቶችን የሚያፋጥን መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የህዝብና የመንግስት አገልግሎቶችን የሚያፋጥን መሆኑን በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
የባንክ አገልግሎቶችን በማፋጠን የማጭበርበር ወንጀሎች እንዲቀንሱ ፋይዳው የጎላ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል።
ባለፉት አመታት ተግባራዊ የተደረገዉ የፋይዳ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ለሀገራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት እየጣለ ነዉ።
በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የአዋሽ ባንክ ሳውላ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዶንጫራ ዶጆ እና የአቢሲኒያ ባንክ ሳውላ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ውድነህ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ሳውላ ቅርንጫፍ የፋይዳ ዲጅታል መዝጋቢ የሆኑት አቶ ዕምነት መስቀለ፥ ፋይዳ በባዮሜትሪክ መረጃዎች የጣት አሻራ እና የፊት ምስልን በመጠቀም የግለሰቦችን ማንነት በትክክል የሚያረጋገጥ ነዉ። ይህም የሀሰተኛ መታወቂያ አጠቃቀምን ለመቀነስ አስችሏል ብለዋል፡፡
ፋይዳ መታወቂያ ዜጎች የባንክ አገልግሎት ሲያገኙ፣ ሲመዘገቡ ወይም የመንግሥት አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ማንነታቸውን በፍጥነት በማረጋገጥ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ እንዲያገኙ የሚያስችል ነዉ።
አገልግሎቱ ከተጀመረ አንስቶም የመንግሥት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተደራሽ እንዲኾኑም አስችሏል።
ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ገብረ አንጃ እና ወ/ሮ ፋጡማ ሁሰን በሰጡት አስተያዬት
ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የህዝብና የመንግስት አገልግሎቶችን የሚያፋጥን መሰረታዊ የሆነ የዲጅታል መሳሪያ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ