የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገልጸዋል።

በሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ የተመራ ልኡክ በማእከላዊ ኢትዮጵያዊ በቡታጀራ፣ በወራቤ ከተማና በተለያዩ ከተሞች እየተሰሩ የሚገኙ የመጠጥ ውሀና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶችን የመስክ ምልከታ እየተደረገ ይገኛል።

በመስክ ምልከታው አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በቡታጀራ ከተማ ከ540 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እተየገነባ የሚገኘው የፍሳሽ ማጠሪያ ፕሮጀክት የመሰክ ምልከታው አንዱ አካል ሲሆን ፕሮጀክቱ ቆሻሻን በማጣራት ዳግም ለአገልግሎት ለማዋል ያግዛል ተብሏል።

ዘጋቢ፡ ዳዊት ዳበራ – ከወልቂጤ ጣቢያችን