የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ክልል አቀፍ ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የ2018 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ክልል አቀፍ ማስጀመሪያ መድረክ በዕምራብ አባያ ወረዳ ቆላ ሞልአቶ ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ወደ ቀበሌው ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የበጎ ፈቃድ ንቅናቄው የአረጋውያን ቤት እድሳት፣ የደም ልገሳ፣ የመረዳዳት፣ የአብሮነትና የአንድነት እሴቶችን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ