ቀጣይነት ያለው የምግብ ዋስትናን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው – የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ቀጣይነት ያለው የምግብ ዋስትናን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝነት እንዳለው ተገለፀ።
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አደረጃጀት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በጮርሶ ወረዳ አካሂዷል፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም ከበደ በባለፉት ክረምት በጎ ሥራ የተለያዩ የድጋፍና የልማት ሥራዎች ማከናወናቸውን ገልጸው በ2015/ 16 በጎ ሥራ አገለግሎት በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡
አያይዘውም ወ/ሮ ለምለም በተያዘው በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ወቅት የምግብ ዋስትናን ችግር ለማስቀረት እየተደረገ ባለው ርብርብ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ከጓሮ አትክልት ጀምሮ በሌሎች ዘርፎችም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሴቶች ሊግ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ነፃነት በቀለ ከዚህ በፊት በተከናወኑ በክረምት በጎ ሥራ ተግባራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
ሴቶች በሁለተናዊ ብልጽግና ጉዞ ውስጥ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚ ዘርፎች በርካታ ሥራዎችን በማከናወን የአቅመ ደካማ እናቶች ቤት ግንባታ፣ የአልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍና በርካታ ተግባራት ማከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየተከናወነ ባለው የሌማት ትሩፋትና አረንጓዴ አሻራ ሥራዎች የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበረ የገለጹት ወ/ሮ ነፃነት ጅምር ሥራዎች አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
በሴቶች በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መክፈቻ ስነ ሥርዓት የተሳተፉ የተለያዩ የሴቶች አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና እናቶች ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ጠይቀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በሴቶች አደረጃጀት የተከናወኑ የግብርና ሥራዎችም ተጎብኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው – ከፍስሀገነት ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ