ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በተካሄደው የሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 በማሸነፍ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምሯል።

ከስድስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚዬር ሊጉ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተገናኙበት ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ወሳኝ የማሸነፊያ ጎል አቤል ያለው በ66ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ዳላንድ ኢብራሂም አቤል ያለው ጥፋት መስራቱን ተከትሎ በ53ኛው ደቂቃ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ከኢትዮጲያ መድህን ጋር የፊታችን ቅዳሜ ሲጫወት ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከነገሌ አርሲ ጋር በመጪው ሀሙስ የሚጫወት ይሆናል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ