ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች

የሩቅ ምስራቋ ሀገር ጃፓን በእግርኳሱ የዓለማችን ሀያል የሆነችውን ብራዚል በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ መርታት ችላለች።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በአቋም መለኪያ ጨዋታ ዛሬ ተገናኝተው ጃፓን ከ2ለ0 መመራት ተነስታ 3ለ2 በማሸነፍ ታሪካዊ ድልን በብራዚል ላይ ተቀዳጅታለች።

በጨዋታው ፓውሎ ሄንሪኬ በ26ኛው ደቂቃ እና ጋብርኤል ማርቲኔሊ በ32ኛው ደቂቃ ጎሎችን በማስቆጠር ሴሌሳዎቹ 2ለ0 እየመሩ ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተው ነበር።

ነገር ግን በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪካቸው ከጥሎ ማለፉ ተሻግረው የማያውቁት ጃፓኖች በሁለተኛው አጋማሽ 3 ጎሎችን አከታትለው በማስቆጠር ውጤቱን ቀልብሰውታል።

በአሰልጣኝ ሃጂሜ ሞዪረሱ ለሚመሩት ጃፓኖች ታሪካዊ የድል ግቦችን የቀድሞ የሊቨርፑሉ አማካይ ታኩሚ ሚናሚኖ በ52ኛው ደቂቃ፣ ኬይቶ  ናካሙራ በ62ኛው ደቂቃ እና አሳዬ ኡኤዳ በ71ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

ጃፓን እና ብራዚል ከአሁን ቀደም 9 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ብራዚል 9 ጊዜ ስታሸንፍ 2 ጊዜ ደግሞ አቻ ነበር የተለያዩት።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ