በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ
በጎፋ ዞን የደንባ ጎፋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱቀ አዶላ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ጉበት ወሳኝ የሰውነት ክፍል ሲሆን ሄፕታይትስ B ጉበትን በመጉዳት እና ከበድ ያለ የጤና እክል የሚያስከትል ቫይረስ መሆኑን ገልጸዋል።
ሄፕታይትስ B በሰውነት ውስጥ መገኘቱ በምርመራ ከተረጋገጠ ወዲያው ተጨማሪ ምርመራዎችን አድርጎ በሀኪም ትዕዛዝ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።
ስለ ሂፕታይትስ B መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች ማወቅ እና መጠንቀቅ ተገቢ ነው ብለዋል።
የደንባ ጎፋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጸ/ቤት የእናቶችና ህጻናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ቡድን መሪ ወ/ሮ አባይነሽ ገ/ህይወት፤ ሄፕታይትስ B በደማችን ውስጥ ተመርምረን እንደሌለ ካወቅን ቅድመ መከላከል ክትባት ስላለው በተገቢው መንገድ ክትባቱን በመወስድ እራሳችንንና የቤተሰባችንን ጤና መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉ አስረድተዋል።
ከእናቶች ወደ ህጸናት ቫይረሱ እንዳይተላለፍ ከወሊድ በኋላ በ24 ሰዓት ክትባቱ መሰጠት እንዳለበት ጠቅሰው በዚሁ ጊዜ ካመለጣቸው በተወለዱ በ14ኛ ቀን ክትባት ማግኘት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ቫይረሱ ምልክት ሳያሳይ በጉበታችን ውስጥ ከመኖር አንስቶ፣ እስከ ጉበት መቆጣት ብሎም በጊዜ በቂ ህክምና እና ክትትል ካላገኘ ለጉበት ካንሰር ሊያጋልጥ ይችላልብለዋል።
የጽህፈት ቤቱ የእናቶችና ህጻናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳዊት ዱካ የስልጠና ሰነድ አቅረበው ውይይት ተደርጎበታል።
ባለሙያው እንዳሉት በሽታ ትኩረት ተሰጥቶ ማስቆም ካልተቻለ ለሞት ሊያጋልጥ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሽታው አስከፊ በመሆኑ የእናቶችና ህጻናትን በበሽታው እንዳይያዙ መከላከያ መንገዶች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ አይናለም ሰለሞን ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ አጠናክረን የምናስቀጥልበት ነው ሲሉ የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
ለአጠቃላይ ትምህርት ጥራት የቅድመ አንደኛ ላይ ትኩረት ማድረግ ሁሉም አካል ሊረባረብ እንደሚገባ ተገለጸ
የሀገር ሉዓላዊ ክብር መገለጫ ለሆነዉ ሰንደቅ ዓላማ ተገቢዉን ክብር መስጠት እንደሚገባ የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ