የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ አጠናክረን የምናስቀጥልበት ነው ሲሉ የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ አጠናክረን የምናስቀጥልበት ነው ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ፈቱዲን ሙዘሚል ተናግረዋል፡፡
በልዩ ወረዳው 18ኛዉ የሰንደቅ አላማ ቀን በፖናል ውይይትና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በወልቂጤ ከተማ ተከብሯል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ፈቱዲን ሙዘሚል እንደተናገሩት ሰንደቅ አላማ ለብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ የከፈታ ዘመን ብስራት ነው ።
የሰንደቅ አላማ ክብረ በዓል ዋነኛው አላማ የህግ የበላይነትን በማክበር እና በማስከበር የፍትህ ስርዓትን ማስጠበቅ እንደሆነ አስረድተዋል።
ለሀገር አንድነት እና ሉዓላዊነት መፅናት አስተማማኝ ብሄራዊ መግባባት ወሳኝ ነው ያሉት አፈ ጉባኤው ሰንደቅ አላማችን የሀገር ሉዓላዊነት እና የህዝባችን የአንድነት መገለጫ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዓሉ ሀገራዊ ስሜትና እንድነት እንዲጎለብት የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የበዓሉ ተሳታፊዎች ናቸው ፡፡
ተሳታፊዎቹ ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ጠንክሮ በመስራት የሀገሪቱ ብልፅግና ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባው ገልፀዋል ፡፡
በበዓሉ የልዩ ወረዳው አመራሮች የፖሊስ አባላት የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው በህብረት የኢትዮጵያ ብህራዊ መዝሙር በመዘመር እና ሰንደቅ አላማ የመስቀል ስነ-ስርዓት ተከናውኗል ።
ዘጋቢ፦ ወለላ ኤልያስ ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ
ለአጠቃላይ ትምህርት ጥራት የቅድመ አንደኛ ላይ ትኩረት ማድረግ ሁሉም አካል ሊረባረብ እንደሚገባ ተገለጸ
የሀገር ሉዓላዊ ክብር መገለጫ ለሆነዉ ሰንደቅ ዓላማ ተገቢዉን ክብር መስጠት እንደሚገባ የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ