የባህል እሴቶችን እና ሀገር በቀል እውቀቶችን በስፋት ማስተዋወቅ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ ።
በዚህ ዙርያ በከልሉ ለማገኙት ሙያተኞች ና ለባለ ድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ባህል ፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈንታሁ ብላቴ የብሄር ብሄረሰቦች ና ህዝቦች ቱባ ባህላዊ ዕሴቶች ሀገር በቀል ዕውቀቶች ና የባህል ተምሳሌቶችን በተደራጀ መልኩ ለማስታወቅ ሚቹ መድረክ ለመፈጠር የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አብራርተዋል ።
በዘርፉ ለተሰማሩት ባለሀብቶች ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ፤ ሙያ ማህበራት ኢንተርፕራይዞች ፣ ወጣቶችና ሴቶች ለልምድ ልውውጥ የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ለመፈጠር እንደሚረዳም አክለዋል ።
የቢሮ ምክትል ኃላፊ ና የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው የባህል ፌስቲቫል፣ ካርኒቫልና ኤግዚብሽን መካሄድ የክልሉን ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በተፈጥሮ የታደሉትን በታሪክ ያካበቱትን ቱባ ባህል ፣ እሴቶች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን የኪነ-ጥበብና የዕደ-ጥበብ ትውፊቶችን ለማስተዋወቅ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ።
ወጣቱ ትውልድ የባህልን ልማታዊ አስተዋጽኦ ግንዛቤ ለመፈጠር በማንነቱ የሚኮራ ትዉልድ ለመፈጠር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
ፌስቲቫል፣ካርኒቫል ና ኤግዚብሽን ስናካሂድ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሉታዊ መጤ ባህሎችን ደረጃ በደረጃ በመቀነስ ብሎም በማስቀረት መሆን እንዳለበት ምክትል የቢሮ ኃላፊ አጽንኦት ሰጥተዋል ።
ስልጠናው በክልሉ ላሉት ከስድቱም ዞኖች ለተወጣጡ ለባህል ሙያተኞች ና ለባድርሻ አካላት የተሰጠ ሲሆን ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹ በሰጡበት አስተያየት በየአካባቢያችን ፌስቲቫል፣ካርኒቫልና ኤግዚብሽን እጅግ የሚጠቅም ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ