የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 10/2017 ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገለፀ
ምክር ቤቱ በዚሁ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አጽንኦት ሰጥቶ እንደሚመክር ተገልጿል።
ከሐምሌ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደው 6ኛ ምርጫ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ታሪካዊ ጉባኤ መሆኑን ነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የገለጹት።
ክልሉ በሁለት ዓመት ቆይታው ባከናወናቸው ተግባራት የታዩ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ያከናወናቸው ስኬቶች ምን እንደሚመስሉ በስፋት ይታያሉ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ።
በጉባኤው ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ በዋና ዋና ጉዳዮች በስፋት ውይይት ይካሄድባቸዋል ብለዋል ዋና አፈ ጉባኤው።
የህዝብን ዘላቂ ሰላም እንዲሁም ልማትን በሚያረጋግጡ እንዲሁም ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ጉባኤው ይመክራል ያሉት የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ፤ በ2017 ለተከናወኑ ስኬቶች ዕውቅናም እንደሚሰጥ አመላክተዋል።
የምክር ቤት አባላት የህዝብ ድምፅ ናቸው ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው፤ ከዕቅድ ጀምሮ መሬት ላይ አፈፃፀሙ በትክክል ስለመውረዱና ህዝቡ የልማት ተጠቃሚ ሰለመሆኑ መከታተል ድርሻቸው እንደሆነም አመላክተዋል።
ከሐምሌ 10 ጀምሮ በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙና የቅድመ ዝግጅት ሥራው መጠናቀቁን ጭምር አቶ አለማየሁ ባውዲ አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ታምሩ በልሁ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ሀገሪቱን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማደረግ ሁሉም አካላት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ
የክልሉን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ በ2018 በጀት አመት በተለያዩ የልማት ዘርፎች የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም