ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሽብርተኛው አይኤስ አይኤስ ቡድን ለማሸነፍ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሽብርተኛው አይኤስ አይኤስ ቡድን ለማሸነፍ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድን ለማሸነፍ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ እያካሄደ በሚገኘው የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ለአንድ ቀን በሚቆየው ስብሰባ የጥምረቱ አባል አገራት የሽብርተኛ ቡድኑን በሁሉም አቅጣጫዎች ለማሸነፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዳግም ቁርጠኝነታቸውን ያረጋግጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከስብስባው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ተገልጿል።