በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘንድሮው የበልግ እርሻ እየለማ ካለው ከ394 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት 77ሺህ ሄክታሩ በኩታገጠም እየለማ ያለ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
በክልሉ ከሚገኙ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ይገኛል።
አርሶ አደር ተስፋዬ የማነህ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ኩጃ ቀበሌ በበልግ ልማት ስራው የተሳተፉ አርሶአደር ናቸው።
አርሶ አደሩ በአካባቢያቸው ከሚገኙ 17 አርሶ አደሮች በጋራ በመሆን ከ78ሄክታር በላይ መሬት ሩዝን በኩታ ገጠም እርሻ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም የኩታ ገጠም እርሻ በአካባቢው እምብዛም የተለመደ ተግባር ያለመሆኑን ጠቁመው የአረም ቁጥጥርና የተባይ አሰሳ በጋራ ለማካሄድ ስራው ምቹ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘንድሮ የተሻሻለ የሩዝ ዘርን በተሟላ ፓኬጅ በማልማት ላይ መሆናቸውን የተናገሩት አርሶአደሩ ከስራቸው በአንድ ሄክታር ከ30 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
ሌላኛው የኩጃ ቀበሌ አርሶአደር ጉችዬ አይተንፍሱ በዘንድሮው በልግ 2ሄክታር መሬት በቆሎና ሩዝን በክላስተር በማልማትና የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሰሩ እንዳሉ ገልጸዋል።
የጉራፈርዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን አስፋው በበኩላቸው በወረዳው በዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ38ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡
በወረዳው በተያዘው የበልግ እርሻ ሩዝ በቆሎ ሰሊጥ በክላስተር በማልማት የአርሶአደሩ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሽዋስ አለሙ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት በክልሉ በዘንድሮው በልግ እርሻ በዋና በዋና ሰብሎች 394ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እየለማ መሆኑን ተናግረዋል።
በበልጉ እርሻ ከ269 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ፣ ከ28 ሺህ ሄክታር በላይ በሩዝ ሰብል የተሸፈነ እንዲሁም ቀሪው በሌሎች ሰብሎች የተሸፈነ መሆኑን አብራርተዋል።
በክልሉ ከለማው የዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ77 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታገጠም እርሻ እየለማ መሆኑን አቶ የሺዋስ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በስራው ከ221ሺህ በላይ አርሶአደሮች የተሳተፉ ሲሆን ከ13.5ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ ፦ጦያር ይማም ከሚዛን ቅርንጫፍ
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ አስታወቀ