የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ15ኛ ዙር በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራሞች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 255 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 276 ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የምረቃ ፕሮግራሙ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ማቲዎስ አኒዮ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ሃዬሶ እና የዩኒቨርስቲው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት እየተካሄ ይገኛል።
ዘጋቢ: ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በክረምት የታየው የበጎ ተግባር ተሳትፎ በበጋ ወራትም በማስቀጠል ደጋፊ የሚሹ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ውብና ጽዱ አካባቢ ለመፍጠር የደን ልማትና ጥበቃን ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ገለጸ
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ