መንግስት ተጠያቂነትን እና የሽግግር ፍትኅን ለማስፈን እየሠራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በድጋሚ አረጋገጡ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ተጠያቂነትን እና የሽግግር ፍትኅን ለማረጋገጥ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚመራ የጋራ ግብረ ኃይል እንደተቋቋመ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
የሽግግር ፍትኅን ለማስፈን መተባበር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም ከኮሚሽነሩ ጋር መክረዋል፡፡
ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ለፕሪቶሪያ የሠላም ስምምነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ÷ ፅሕፈት ቤታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ሠላምን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረትም ፅሕፈት ቤታቸው እንደሚደግፍ አስምረውበታል።

More Stories
የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተቋሙ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መነሻ ያሉባቸውን ክፍተት በአዲሱ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመሻገር በልዩ ቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የየዞኑ የትምህርት አመራሮች ገለፁ
ኒውካስል ዩናይትድ ብሩኖ ጊማሬሽን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናል ለመሸጥ ተስማማ