የኢድ  አል ፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የኢድ  አል ፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ኮሚሽኑ ለመላው የእስልምና  እምነት ተከታዮች ለ1ሺህ 446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፏል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከልና ትራፊክ ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብረሃም ቲርካሶ እንዳሉት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢድ አል ፈጥር በዓል በአደባባይ በድምቀት የሚከበር በመሆኑ በዓሉን  ያለምንም ጸጥታ ስጋት ማክበር እንዲቻል በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል ።

የክልሉ ፖሊስ የሕብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ  ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋረ በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል ።

በዓሉን ለማክበር በሚያደርገው በማንኛውም እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል ።

በተለይም  ከእሳትና ከኤሌክትሪክ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማደረግ እንደሚገባም ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል ።

ዘጋቢ :ታምራት አለሙ -ከሆሳዕና ጣቢያችን