ከገበያ ትስስር፣ ከመሠረተ ልማት ውስንነት እንዲሁም ከማስፋፊያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ውስንነቶች እንዲቀረፉላቸው በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ጠይቀዋል።
ሰሞኑን በክልሉ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ በተደረገው ምልከታ በተኪና በኤክስፖርት ምርቶች ረገድ ተስፋ ሰጪ ጅምሮቾ መኖራቸውም ተመላክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፤ በጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አሪ፣ ወላይታና ጌዴኦ ዞኖች ባደረገው የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምልከታ፤ በክልሉ በርካታ ባለሀብቶች ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስ የጀመሩት የማምረት ስራ ተስፋ ሰጪ ጅምር መኖሩን አመላካች ነው።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከማስቀረት ባለፈ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን በአምራች እንዱስትሪዎቹ ተጠቅሷል።
እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥረዋል።
ከገበያ ትስስር፣ ከመሠረተ ልማት ውስንነትና ከማስፋፊያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ተግዳሮቶች እንዲቀረፉላቸው በዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪያሊስቶች ጠይቀዋል።
የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎችም የተሻለ አቅምና እውቀት እንደገበዩና ከራሳቸው አልፎ ቤተሰብ ማስተዳደር እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ አማካሪ ዳይሬክተርና በክልሉ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አስተባባሪ አቶ ገለቱ ገነሞ፤ እንዱስትሪዎችን ማበረታታት እንደሚያስፈልግና አምራቾችም በሳይንሳዊ ምርምር በመደገፍ የማምረት አጠቃቀም ልኬታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።
በዘርፉ እየታዩ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የጋራ ስራ በመስራት ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እንደክልል እየተሰራ ነው ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቦጋለ ቦሼ፤ እንደ ክልል ተወዳዳሪና አምራች እንዱስትሪን ከመፍጠር ረገድ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንና እንደ ሀገር ትኩረት የተሰጠውን ተኪ ምርትን በማምረት ረገድ ባለፉት ስድስት ወራት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
የኤክስፖርት ምርት በማምረት በኩልም ተስፋ ሰጪ ጅምር ስራዎች መኖራቸውንና በዚህም ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል ዶ/ር ቦጋለ።
ዘርፉ ዘላቂ እንዲሆን ከምርምርና ስርጸት አኳያ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየተሰራ እንደሚገኝና ውስንነቶችንና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ቀሪ ተግባራት መኖራቸውንም ጭምር ገልጸዋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውንና የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ የስራ እድል የመፍጠሩን ሂደት በይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚናን በተመለከተ የጋራ ውይይት በጂንካ ከተማ ተካሄደ
ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ
የከተሞችን የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በማከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ