የክህሎት ዘርፍ የልማት ሞተር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረትና የስራ ፈጠራ ዋንኛ ምንጭ መሆኑ ተገለፀ

‎

‎የክህሎት ዘርፍ የልማት ሞተር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረትና የስራ ፈጠራ ዋንኛ ምንጭ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የስርዓተ ሰነዶች እና አዳዲስ ኢንሼቲቮች አተገባበር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

‎

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የክህሎት ዘርፍ አመራሮች እና ለኮሌጅ ዲኖች የስርዓተ ሰነዶች እና አዳዲስ ኢንሼቲቮች አተገባበር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ነው።

‎

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የክህሎት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ስልጠናው ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎የክህሎት ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት ደጋፊ ብቻ ሳይሆን የልማት ሞተር፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር መሰረትና የስራ ፈጠራ ዋንኛ ምንጭ መሆኑን ገልፀዋል።

‎

‎የማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምራት ተስፋሁን በበኩላቸው፤ ስልጠናው ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ ለመታጠቅና ውጤታማ ተግባር ለማከናወን ወሳኝ ነው ብለዋል።

‎

‎ዛሬ የጀመረው ይህ ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስለመሆኑም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‎

‎ዘጋቢ፡ ሙባረክ አክመል – ከወልቂጤ ጣቢያችን