ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) ተናገሩ።

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) ተናገሩ።

28ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጤና ተቋማት ላይ በተሰራው ሪፎርም በሁሉም ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲኖር ተደርጓል ሲሉ ነው ዶክተር መቅደስ የገለጹት።

የወባ በሽታን ለመከላከል በተወሰደው ርምጃ 58 ከፍተኛ ጫና በነበረባቸው ወረዳዎች ላይ በተሰራ ስራ የሞት ምጣኔን ከ50 በመቶ መቀነስ እንደተቻለ አመልክተዋል፡፡

በቅድመ መከላከል ስራ የማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታን ለመከላከል በተደረገው ርብርብ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚደርሱ ሴቶች የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም በእናቶች ጤና ላይ በተሰራው ስራ የእናቶችን ሞት መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ጤናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተያዘው ሀገራዊ ሪፎረም 226 የመንግሥት የጤና ተቋማት የካርድ ሥርዓታቸውን፣ 11 ሺህ የሚሆኑ የጤና ኬላዎች ደግሞ የመረጃ አያያዛቸውን ወደ ዲጂታላይዝ መሆን እንዳለበትም ነው የተናገሩት።

ዘጋቢ፡ ብሩክ አማረ