የሲዳማ ክልል የግብርና ኢንቨስትመንት ፎረም በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
ፎረሙ በርካታ ኢንቨስተሮችን ያሳተፈ መሆኑም ተገልጿል።
በሲዳማ ክልል የግብርና ዘርፍ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ፣ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠርና ባለሀብቶችን ወደ ክልሉ ለመሳብ ያለመ የሲዳማ ክልል የግብርና ኢንቨስትመንት ፎረም 2019 በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ፎረሙ በግብርና ዘርፍ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማጠናከርና የልማት አጋርነትን በማስፋፋት ለክልሉ የግብርና ልማት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ከግብርና ምርት ዕድገት፣ ምርታማነትን ከማሳደግ፣ ከምርት ማቀነባበርና ከገበያ ትስስር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ በክልሉ ያሉ የግብርና ሀብቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ትርፍ እንዲቀየሩ የሚያግዝ መድረክ ነው።
ፎረሙ በሐዋሳ ከተማ የተጀመረ ሲሆን እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
በፎረሙ ላይ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የግብርና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሠረት ፎረሙ ከጥቅምት 28 እስከ 29 ቀን 2019 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ዘገቢ፡ መሐሪ አድነው

More Stories
ወቅቱን የዋጀ የጤና ስርዓት ለመገንባት የጋራ ተግባቦት የምንፈጥርበት እና በዘርፉ ያለንን ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት ነው – ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
28ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል
የእንሰት ተክል ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በተመለከተ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሰራታቸውን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለፀ