በአካባቢው ሊለሙ የሚችሉ ጸጋዎችን በመጠቀም አካባቢውን መቀየርና ለሀገራዊ ዕድገት አበርክቶ እንዲኖረው ለማስቻል አስፈላጊ ጥረቶች እንደሚያደርጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አስታወቁ
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት በጂንካ ከተማ ከኣሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።
በመድረኩ የኣሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች አቶ አፌዶ ወርቁና አቶ ማዕከል ማሊኮ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በአካባቢው በርካታ የተፈጥሮ ጸጋዎች ያሏቸው መሆኑን በዝርዝር አንስተዋል።
ቢሆንም ሀብቶቹን ከመጠቀም አንጻር ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቅሰው በአግባቡ እንዲለሙ በሚያስችል መልኩ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
ከዚህ አኳያም ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ውይይት መደረጉ በቀጣይ በሚያስቀምጡት የስራ መመሪያ መሰረት በአካባቢው የተሻለ ለውጥ ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ የሀገር ጌጥ በሆኑት ሁለት ዞኖች በመገኘታቸው ኩራት እንደተሰማቸው ጠቅሰው እነዚህ ዞኖች የክልሉ 50 በመቶ ብዝሃ ማንነትን የያዙ የሀገር ሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ታታሪና ትጉህ ህዝቦች፣ ሊለሙ ከሚችሉ የሀገር ሀብቶች ጋር የታደሉ ዞኖች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
እነዚህን ሀብቶች ለማልማትም የመደመር መንግስትን መርሆች በመከተል ለአካባቢው ለውጥ የትኛውም አይነት ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአንድ ማህበረሰብ ቋንቋ ለትውልድ እንዲተላለፍ እና በጽሑፍ እንዲበለጽግ የቋንቋ ሰዋሰው ጥናት ወሳኝ ሚና አለው – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህልና ስፖርት ቢሮ
ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ጂንካ ከተማ ገቡ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው