በዘንድሮው የምርት ዘመን ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ እየሠራ መሆኑን በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በወረዳው የቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ እንዳለ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የምርት ዘመን 3 ሺህ ቶን እሸት ቡና በመሰብሰብ ጥራቱ የተጠበቀ 510 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ ነው።
በሳርማሌ ወረዳ በሚገኙ ሰባት የእሸት ቡና መፈልፈያ እና አምስት የግብይት ማዕከላት ውስጥ ጥራቱ የተጠበቀ የቡና ግብይት ሥርዓት እንዲከናወን ከወረዳው የቡና ጥራት ቁጥጥር ግብረሀይል ጋር በትብብር እየሠሩ እንደሚገኙም ነው አቶ ታሪኩ የገለጹት።
በጉሙሬ ቀበሌ ሙላ የእሸት ቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ የእሸት ቡና ጥራት ቁጥጥር ኃላፊ አቶ ማርቆስ መንገሻ በበኩላቸው፤ የቀላ ቡና ብቻ ተለቅሞ በጊዜ ወደ መፈልፈያ ጣቢያ መቅረብ እንዳለበት በማስታወስ በተገቢ ጥንቃቄ፣ ከኢንዱስትሪ እስከ ማዕከላዊ ገበያ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ አዘጋጅተው እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
እሸት ቡና በባህሪው ከቆሻሻና ከባዕድ ነገር ንክኪ ነፃ መሆን እንዳለበትም አቶ ማርቆስ አስረድተዋል።
ካነጋገርናቸው አርሶ አደሮች አቶ እንግሊዜ ኢሳቱ እና ዮሐንስ ሶንካ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መሰረት ከዛፍ ላይ የቀላ እሸት ቡና ብቻ በመልቀም በጊዜ ወደ ኢንዱስትሪ እና የተመረጡ ግብይት ማዕከላት እንደሚወስዱ ነው የገለጹት።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን።

More Stories
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማፅናት እና ለማበልፀግ የምንሰራበት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)