ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ መስከረም 28/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው፣ ዛሬ መሾም ሸክም መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በስብሰባው የካቢኔዎች ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀርቦ ጸድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ ካቢኔዎቻቸውን ከተመረጡበት መስፈርት ጋር ሲያቀርቡ ኢትዮጵያ እያመጣች ያለውን ዕድገት ተገንዝበው የሚያስፈጽሙ፣ በቀጣይ የተዘጋጀውን ታላቁን የመደመር ስትራቴጂ እውን እንዲሆን የሚተጉ፣ በሕዝቡ ዘንድ የሚነሳውን ሙስና የሚጸየፉና የሚከላከሉ እንዲሁም ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን የሚሰሩ እንዲሆኑ ጥረት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የሚመረጡ ካቢኔዎች ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው እንዲሁም መሾም ሸክም መሆኑን እንዲገነዘቡ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡
አያይዘውም ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበትና የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ለማበልጸግ፣ ብሎም ወደ ሥልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት የሥራ መስክ እንደሆነ መገንዘብ አለባቸው በማለት አሳስበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዕጩ ካቢኔዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበው የካቢኔዎቹ ሹመት ጸድቋል፡፡
ዘጋቢ፡ ኢያሱ ታዴዎስ

More Stories
ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማፅናት እና ለማበልፀግ የምንሰራበት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው በሙሉ ድምጽ ጸድቋል
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ የካቢኔ አባላትን ተቀብሎ አጸደቀ