የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቱሪዝም ቢሮ 2018 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ግምገማ እና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል
የወላይታ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ ረዳት ኘሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፤ ቱሪዝም ከብዝሃነት ኢኮኖሚ አንዱ በመሆኑ በአካባቢው የሚገኙ የማይዳሰሱ እና የሚዳሰሱ ሀብቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ በተከናወነው ሰፊ ስራ መነሻ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ቱሪስቶችን ለመሳብ የቱሪዝም ዘርፍን በማስፋፋት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ ይበልጥ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንቱ መልኩ፤ መንግስት የቱሪዝም ዘርፉን በማዘመን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና 2019 ዕቅድ በቢሮው ማለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የአርሶአደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ለግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግርና ምርታማነት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተገለፀ
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ