የወላይታ ብሄር የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም መካሄድ ጀምሯል

‎ሀዋሳ፡ መሰከረም 09/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወላይታ ብሄር የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በጉተራ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

‎ሲምፖዚየሙ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል በሚከበርበት ዋዜማ ላይ የሚካሄድ ነው።

‎የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም መድረክ የተለያዩ የወላይታ ባህላዊ ጭፈራና ሀያ ሌኬ ጫዋታ እና በሲምፖዚየሙ ጥናታዊ ፅሑፍ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

‎በመድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ፈቃዱ ማትዮስ – ከዋካ ጣቢያችን