የፍትህ ስርዓት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የፍትህ ስርዓት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ

ባህላዊ ዕሴቶቻችንን በመጠቀም የፍትህ ስርዓት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ፍርድ ቤቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህላዊ ፍርድ ቤት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ አፈፃፀም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

‎የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሳሙኤል በፍቃዱ በወጣው አዋጅ መሠረት ወደ ተግባር ለመግባት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ አፈፃፀሙ አበረታች ነው ብለዋል፡፡

‎‎የባህላዊ ፍ/ቤት መቋቋም ማህበረሰቡ የፍትህ አሰጣጥ አገልግሎት በአካባቢያቸው ከማግኘትም በተጓዳኝ የባህላዊ ዕሴቶቻችን ማጎልበቻ ዘዴ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል::

የባህላዊ ፍ/ቤት መቋቋም የመደበኛ ፍ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን የሚያቀላጥፍ መሆኑን በማንሳት በተቀመጠው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት አገልግሎቱን ለማስጀመር እየሰሩ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች አስረድተዋል::

‎ዘጋቢ፡ አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን