በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከጅምሩ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ
ይህ የተገለፀው የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር በይፋ በተጀመረበት ወቅት ነው።
የመማር ማስተማር መርሃግብሩን ያስጀመሩት የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፤ በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከጅምሩ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የትምህርትን ስብራት ለመጠገን እንደሀገር የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ከወዲው መዘጋጀት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የመማር ማስተማር ሥራቸውን በአግባቡ መጀመራቸውን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የጠቀሱት አቶ ብዙአየሁ፤ በስነ-ምግባር የታነፀ፣ ስለ ሀገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅም በተገቢው መንገድ የሚረዳ ትውልድ ለማፍራት በአፅንኦት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በይርጋጨፌ ከተማ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች የዛሬው ዕለት የመማር ማስተማር ተግባር አጀማመር ሂደታቸው በዞኑና በከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዶባቸዋል።
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ያለፈውን በጀት ዓመት ተግባራት በፖሊስ ተቋምና በግለሰቦች ደረጃ በመገምገም ቀጣይ የስራ አቅጣጫን መለየት እንደሚገባ ተገለጸ
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ በሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል እያከናወነ የሚገኘውን አበረታች ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ