ጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” በቡርጂ ዞን በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ

ጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” በቡርጂ ዞን በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ

‎ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የኅብር ቀን” በቡርጂ ዞን በተለያዩ የመረዳዳት እና መከባበርን በሚያጠናክሩ መርሐ ግብሮች ነው የተከበረው።

‎መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የቡርጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሉላ ግና የኅብር ቀንን ስናከብር ከጥላቻ ንግግር እና ከተሳሳተ መረጃ ተላቀን፣ ብዙም አንድም ሆነን በወንድማማችነት መንፈስ ማክበር ይገባናል ብለዋል።

‎የህብር ቀንን ስናከብር በመረዳዳት፣ በመከባበር እንዲሁም በአንድነት ልናከብር ይገባል ሲሉ አክለዋል።

‎በመድረኩ በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል የሚለውን የዞኑ ፍትህ መምሪያ የህግ ባለሙያ በሆኑት አቶ ቡርጄ ሻደኤ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

‎ከተሳታፊዎች መካከል በቡርጂ ዞን ደረጃ እየተበራከተ ያለው “የፌክ አካውንት” ጉዳይ፣ የሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር መብዛት አሳሳቢ እንደሆነ አንስተው፣
‎የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር መንግስት ሊቆጣጠረው እንደሚገባ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

‎በዞኑ አንዳንድ “በሬ ወለደ” የሆኑ መረጃዎች እየተሰራጩ የአከባቢውን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ በመሆኑ ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይ መንግስት ክትትል እያደረገ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

‎በተጨማሪም አቅመ ደካማ ለሆኑ እና ረጂ ለሌላቸው ተማሪዎች የበዓል መዋያ እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

‎በመድረኩ የዞን፣ የሶያማ ዙሪያ ወረዳ እና የሶያማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ በዞኑ የሚንቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚዲያ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

‎ዘጋቢ: ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያች