በዲላ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

በዲላ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

‎ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዲላ ከተማ አስተዳደር “ከህብር የሚመነጭ ኃይል ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የህብር ቀን በድምቀት ተከብሯል።

‎በዝግጅቱ ለይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)÷ ከተማችንን ውብ፣ ጽዱ እና ማራኪ ለማድረግ ያከናወንናቸው ተግባራት በህብርና በአንድነት ስለቆመን የመጣ ውጤት ነው ብለዋል።

‎አክለውም ውጤቱን ለማስቀጠል ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ታሪኩ በየነ በበኩላቸው ቀኑ በህብርና በአንድነት ቆመን በቀጣይ ጊዜ በጋራ ለመሥራት እና በወንድማችነት እና በብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ብሎም በፍቅር በጋራ ለመኖር ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል።

‎በዓሉን በማስመልከት የደም ልገሳ መርሃ-ግብርን ጨምሮ የመማሪያ ደብተር ድጋፍ በማድረግ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያንጸባርቁ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

‎በመርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ሥራ ኃላፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

‎ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን