የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤት ርክክብ አድርጓል
በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የተገኙት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛው የመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን በርካታ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች በመሣተፍ የከተማውን ህዝብ ተጠቃሚ እያደረገ እንዳለ አስታውሰው እየተደረገ ላለው አጋርነት ዩኒቨርሲቲውን አመስግነዋል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ፤ ዩኒቨርሲቲው በክረምቱ ወራት በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው ይህም ከዩኒቨርሲቲው ሦስቱ የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠው የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጉዳዮች ከዩኒቨርሲቲው ጋር እያደረገ ላለው ትብብር አመስግነዋል።
ቤት የተገነባላቸው አቅመ ደካሞችም ከዚህ ቀደም ይኖሩበት የነበረው ቤት በክረምት በዝናብ በበጋ ደግሞ በፀሐይ ሙቀት ይጨናነቁ እንደነበር አስታውሰው ችግራቸውን በመረዳት ዩኒቨርሲቲው ስላደረገለቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤት ርክክብ አድርጓል

More Stories
በዲላ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
ብዝሃነታችን የማንነታችን ጌጥ እና የአብሮነታችን ከፍታ ነው ሲል የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ
የ2019 ዘመን መለወጫና የመስቀል በአል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የፀጥታ ሀይሉ በመቀናጀት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ