በዞኑ የቱሪስት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የኮንሶ ዞን ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ‎

በዞኑ የቱሪስት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የኮንሶ ዞን ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ
‎
‎በ2018 በጀት አመት ከ3 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል።
‎
‎የኮንሶ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ዝናቡ ገሠሠ በ2018 በጀት አመት 438 የሀገር ውስጥና 2 ሺህ 851 የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን ከዚህም 4 ሚሊየን 550 ሺህ ብር መገኘቱን አስታውቀዋል።
‎
ከ2017 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የጎብኚ ቁጥር የጨመረ እና አፈፃፀሙም 168 በመቶ የገቢ ብልጫ እንዳለው አመላክቷል።
‎
‎በሀገር ደረጃ የተደረገው የፖሊሲ ለውጥ፣ የዞኑ ሰላም መሆን አልፎም ቱሪዝሙን ወደ ፊት የማምጣቱ ተግባር ትልቅ መነቃቃት በመፍጠሩ የቱሪስቱንና የገቢ አቅም እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አቶ ዝናቡ ገልጸዋል።
‎
‎በቀጣይ የጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ መዳረሻዎቹን ምቹና ሳቢ እንዲሆኑ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አዳዲስ ስትራቴጂዎች መቀረጻቸው ተጠቁሟል።
‎
‎በሀገራችን የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ከሀገር አልፎ ለዓለም በይበልጥ ለማስተዋወቅ የሁሉም ድርሻ የጎላ በመሆኑ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የመምሪያው ኃላፊ አጽንኦት ሰጥተዋል።
‎
‎ዘጋቢ: ተዋበች ዳዲ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን