የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ6ኛ ዙር በተለያዮ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በደማቅ ስነ-ስርአት በማስመረቅ ላይ ይገኛል
በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ በመመረቅ ለይ የሚገኙት የእንስሳት ህክምና ተማሪዎችን ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚያስመርቃቸው የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ እና የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና የጂንካ ዩኒበርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የዩኒበርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ የዩኒበርሲቲው የቦርድ አባላት፣ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና የፌደራል፣ የክልልና የዞን ልዩ ልዩ አመራሮች፣ ተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ታድመዋል፡፡
ዘጋ፡ ተመስገን ሰይፉ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ