የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በስፔሻሊቲ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 479 ተማሪዎችን በዋናው ግቢ እያስመረቀ ነው
ከዩኒቨርሲቲው የ17ኛው ዙር ጠቅላላ ተመራቂ ተማሪዎች መከከል 539 ሴቶች ሲሆኑ 940 ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተመላክቷል።
ከዕለቱ ተመራቂዎች መካከል 45 የሕክምና ዶክተሮች እና 15 ስፔሻሊስት ሐኪሞች መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል እና የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዳዊት ሃዬሶ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ዘጋቢ: ሙጂብ ጁሃር – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ