የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢትዮጵያ ገፅታዋን የቀየረችበትና የአየር ንብረቷ እንዲስተካከል ያደረገ አመረቂ ተግባር መሆኑ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 07/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢትዮጵያ ገፅታዋን የቀየረችበትና የአየር ንብረቷ እንዲስተካከል ያደረገ አመረቂ ተግባር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸው ከፍተኛ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው የዞኑ አመራሮችና ጎብኝት የተደረገላቸው አካላት ገልፀዋል።
ክልሎችና የአካባቢው መስተዳድሮች የአካባቢን ፀጋ ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ዜጎች የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ እየተሰራ ያለውን ተግባራት በቤንች ሸኮ ዞን በተደረገው ጉብኝት መመልከታቸውን የኢፌደሪ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ተናገረዋል።
በዚህም የአረንጓዴ አሻራው ልማት ኢትዮጵያ በዓለም ገፅታዋን የቀየረችበትና የአየር ንብረቷ እንዲስተካከል ያደረገችበት አመረቂ ሥራ የተከናወነበት ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል።
ከሰሞኑ ሀገር አቀፍ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በቤንች ሸኮ ዞን የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ያደረጉት ጉብኝት ለአመራሩም ሆነ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸውም አመላክተዋል።
የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ኬና፣ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እና የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ ካረካ በሰጡት አስተያየት ጉብኝቱ ለቀጣዩ ሥራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተላቸው ተናገረዋል።
ለክልሉ 2ሺህ ኩንታል ሾኔ በቆሎ እና 7 መቶ ኩንታል ሩዝ ምርጥ ዘር ማሰረከባቸውን አቶ ገመቹ ደግፌ የኩጃ ዘር ብዜት እርሻ ኃላፊ የገለፀ ሲሆን የሴካ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበርም የተቀናጀ ግብርናን እያከናወነ ከመሆኑም ባለፈ በፌደራል ሚነስቴር መስሪያ ቤት መጎበኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናገረዋል።
የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋቶች፣ የክረምት በጎ ሥራ እንዲሁም የኤክስፖርት ምርቶች ተጎብኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ