በኮሬ ዞን ምክር ቤት 18ኛው የሰንደቅዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዕለቱ “ሰንደቅዓላማችን ለኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን ዋና አፈጉባዔ ወይዘሮ አካላት በቀለ፥ የእንኳን አደረሰን መልዕክት በማስተላለፍ የኢትዮጵያ ስንደቅዓላማ የሚከበረው ለሀገሪቱ ሉኣላዊት መስዋዕትነት የከፈሉትን በማስታወስ ነው ብለዋል።
አክለውም የባዲራ ስነ-ስርዓት ሁሌም በማሰብ እንደየሁኔታው ሰዓታት የተለያዩ ቢሆንም ሁሉንም በተገቢ ጥንቃቄ ማውጣትና ማውረድ እንደሚጠበቅም አስታውሰዋል።
ከስነ-ስርዓቱ ተካፋዮች መካከል ወይዘሮ ፍሬህይወት ቢተው እና አቶ አስረስ ዘውዴ ስንደቅዓላማ የሀገር ሉአላዊነት መገለጫ መሆኑን በመግለጽ፥ ዕለቱን ጠብቆ ማክበር ብቻ ሳይሆን ለልጆቻቸውም እንደሚያስተምሩ ተናግረዋል።
የባንዲራ ቀን አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ ስለ ሀገር አንድነት እና ልማት በኮሬ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉቀን በቀለ አማካኝነት የዕለቱ ተሳታፊዎች ቃለመሀላ ፈጽመዋል።
አዘጋጅ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን
More Stories
18ኛዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በቦንጋ ከተማ ተከበረ
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም
የቀን 6፡30 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ – ቀጥታ ስርጭት