የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል
ሀዋሳ፡ ህዳር 17/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ምሽን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

More Stories
የግብርናው ዘርፍ ለጂዲፒ ካለው ድርሻ አኳያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ተበልጧል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ማወክ ለሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች
ሠላምና ይቅርታን በሚመለከት