በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 5 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 5 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ሦስተኛ ቀን ውሎ ዛሬ በሚደረጉ አምስት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይቀጥላል።

በዛሬው መርሃ ግብር ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ አራት ጨዋታዎች በአንድ ጀምበር የሚደረጉ ሲሆን፥ በተለይም የሻቪ አሎንሶው ቡድን ቼልሲ ከሜዳው ከሰንደርላንድ እንዲሁም ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ከሜዳቸው ውጪ የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪውን ቀልብ የሳቡ ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው።

በተመሳሳይ 11 ሰዓት ብራይተን ከብረንትፎርድ፣ እንዲሁም ኢፕስዊች ታውን ከቦርንማውዝ ጋር ነጥብ ለመንጠቅ ይፋጠጣሉ።

የዕለቱ ታላቅ ጨዋታ ምሽት 1ሰዓት ከ30 ላይ በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም ይካሄዳል።

በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው እና ከቀደመ ጥንካሬው የራቀው ማንቼስተር ዩናይትድ፣ ጠንካራውን አስቶንቪላን በሜዳውና በደጋፊው ፊት አስተናግዶ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ብርቱ ትግል ያደርጋል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ