በርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን የተመራ ህዝባዊ ውይይት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ላይ በዞኑ ባሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ህዝባዊ ውይይትና የአመራር ትውውቅ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።
የክልል ብዝሃ ከተሞቸ መካከል አንዷ በሆነችውና የርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ህዝባዊ ውይይት ከዞኑ ሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ቀደም ሲል በቦንጋ ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎች በክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በዚህም የቦንጋ አየር ማረፊያ፣ የክልሉ ቢሮዎች ግንባታ፣ የቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትና የቦንጋ ማረሚያ ተቋምን እና አጠቃላይ የልማት ስራዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።
መድረኩ በዞኑ ከሚገኙ ሶሥት ነባር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ተወያዮችም በቦንጋ ከተማ ተገኝተዋል።
የመደመር መንግስት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማድመጥ ምላሽ መስጠት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን መሰረት ያደረገ ህዝባዊ ውይይት ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤታ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዳንኤል ያዙ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ

More Stories
የከብቶቻቸውን ዝርያ በማዳቀል ከወተትና ሥጋ ምርት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በኣሪ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለፁ
የብሩኖ ፈርናንዴስ መኖሪያ ቤት ተዘረፈ
ወጣቶች የስራ ጠባቂነት አመለካከትን በማስወገድ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በመሰማራት ለሀገራቸው እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው ተጠቆመ