የመደመር መንግስት የህዝብን ጥያቄ በማድመጥ ምላሽ መስጠትን መነሻ ያደረገ የውይይት መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ነው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት ከዳውሮ ዞን ከተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር በታርጫ ከተማ የትውውቅና ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በዞኑ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችና በቀጣይ የሚኖሩ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች የዕለቱ ዋነኛ የውይይት ርዕሰ ጉዳይ ሲሆኑ ከተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የውይይት መድረኩ በትናንትናው ዕለት በዞኑ ታርጫ ከተማ የተደረገውን የልማት ጉብኝት መነሻ ያደረገና ግንባታቸው የተጓተቱ ልዩ ልዩ ስራዎች በአፋጣኝ የሚጠናቀቁበት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
በውይይት መድረኩ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ በዛብህ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ ከዞኑ የተወጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ሌሎች የክልሉ አስተባባሪ አካላት እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ

More Stories
በንግዱ ዘርፍ ያሉ አቅሞችን በመጠቀም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ
የቡናን ጥራት በመጠበቅ ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተናገሩ
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚዲያ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ