ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከቀቤና ልዩ ወረዳ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው

“በመደመር መንግስት ህብረተሰብ አቀፍ” የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከቀቤና ልዩ ወረዳ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሚኖራቸው የምክክር መድረክ በልማት፣ በሰላም፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ሰሞኑን በክልሉ ከተለያዩ ዞኖች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)፤ የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉና የልዩ ወረዳው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን