በ248 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 3 የሕክምና አገልግሎት ማዕከላት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመረቁ

በ248 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 3 የሕክምና አገልግሎት ማዕከላት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመረቁ

‎
‎በ248 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 3 የሕክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)፤ በተገኙበት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመርቀው በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

‎
‎ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት ማዕከላት የቃጠሎ ሕክምና፣ የውስጥ ደዌ ሕሙማን ተኝቶ ሕክምና እና ከወረቀት ነፃ የመረጃ አገልግሎት ማዕከላት ሲሆኑ በኖርዌይና በስዊድን በሚገኙ አጋር ድርጅቶች 150 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የቃጠሎ ሕክምና ማዕከል አንዱ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል ።

‎
‎ማዕከሉ በቃጠሎ ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች የፕላስቲክ ሰርጀሪን ጨምሮ የተለያዩ የላቁ የሕክምና አገልግሎቶችን ከመስጠት በተጨማሪ ከተፈጥሮ አፈጣጠር ጋር ተያይዞ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ሕፃናትና አዋቂዎች የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።

‎
‎በምረቃ መርሀ-ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)፣ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አመራሮች፣ የክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች እየታደሙ ይገኛሉ ።

‎
‎ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን