የመንግሥት የባለፉት ዓመታት ሪፎርሞች ኢኮኖሚው አይበገሬ ሆኖ እንዲቀጥል እና ሀገር እንዲጸና ወሳኝ ሚና መጫወቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ በዓለም ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት፣ ውድድር እና ፉክክር የንግድ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።
በተዛባው የንግድ ስርዓት ውሰጥ ነዳጅ እና ማዳበሪያን ጨምሮ ወሳኝ በሚባሉ ምርቶች ላይ እጥረት መከሰቱን አመልክተዋል።
በምርት ማጋበስ ምክንያት በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሬ መታየቱንም ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የእድገት መንገራገጭ እንዳለ እና የኑሮ ወድነት ጫና መጨመሩንም ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መንግሥት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገበራቸው ሪፎርሞች ኢኮኖሚው አይበገሬ ሆኖ እንዲቀጥል እና ሀገር እንዲጸና ማስቻሉን ጠቁመዋል።

More Stories
የግብርናው ዘርፍ ለጂዲፒ ካለው ድርሻ አኳያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ተበልጧል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ማወክ ለሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች
ሠላምና ይቅርታን በሚመለከት