ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ባለው 7ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱ ጥያቄዎች፡-
👉የመደመር መንግስት እስከ 2050 ድረስ የሚዘልቅ የ25 ዓመት ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር የመደመር መንግስት ታላቁ ስትራቴጂን በምን መልኩ እውን ለማድረግ እየሰራ ነው? ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል?
👉በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላም እጦት ጋር በተያያዘ ብዙ ግጭቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ግጭቶችን ከማርገብ አንጻር መንግስት ምን እየሰራ ነው? ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል?
👉ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ላይ ትገኛለች፡፡ ከዚህ አንጻር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እስካሁን ያበረከተው አስተዋጽኦ ምንድነው? ዕዳ ከመክፈል አንጻርና የኢኮኖሚ ግሽበትን ለማስተካከል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ምን ይመስላሉ?
👉የአካባቢ ምርጫን በተመለከተ ላለፉት 13 እና 14 ዓመታት የአካባቢ ምርጫ አልተካሄደም፡፡ በዚህም ምክንያት የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሌሎችም ዜጎችን ተጠቃሚ የማያደርጉ ጉዳዮች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ስለዚህ የአካባቢ ምርጫ መካሄድ ስላለበት በቀጣይ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ቢገለጽ?
👉የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በ2007 ዓ.ም እና 2017 ዓ.ም መካሄድ ሲገባው አልተካሄደም፡፡ የበጀት ቀመርና የበጀት ድልድል ለማድረግ ስለሚያስችል መቼ እንደሚካሄድ ቢገለጽ?
👉በሀገራችን የሰብዓዊ መብቶች እየተከበረ ቢሆንም አሁንም የዜጎች መብት ጥሰት አለ፡፡ የዜጎች የመኖር መብት አስጊ ሆኗል፡፡ በሕይወትና በቁስ ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ለምን ችላ አለ?
👉የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እና ሌሎችም የሜጋ ፕሮጀክቶች ወቅታዊ አተገባበር ምን ይመስላል?
ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

More Stories
የግብርናው ዘርፍ ለጂዲፒ ካለው ድርሻ አኳያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ተበልጧል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ማወክ ለሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች
ሠላምና ይቅርታን በሚመለከት