የአዲስ ዓመት ዋዜማ ተጨማሪ ብስራት የሆነዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አራተኛ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተዉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተዉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ ሁሉንም ፀጋዎችና አቅሞች አስተባብሮ ማልማት አስፈላጊ ነዉ ያሉት አቶ እንዳሻዉ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነትንና አብሮ የመልማት መርህን መሠረት አድርጋ የጀመረችዉ አቅጣጫ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማፋጠን መላዉን ህዝቦች በማሳተፍ ለጀመረዉ ጥረት መላዉ ህብረተሰብ የተለመደዉን ታላቅ ድጋፉን እጠናክሮ እንዲቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በጋራ መልማትን መሠረት ያደረገ፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ የዉጭ ጉዳይና ዲፕሎማሲ አቅጣጫ የምትከተል ሀገር መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ፣ ይህንን አቅጣጫ መሠረት አድርጎ መንግስት ለሚያደርገዉ ጥረት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና መላዉ የክልሉ ሕዝቦች ከመንግሥት ጎን የቆሙ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።

የአዲስ ዓመት ዋዜማ ተጨማሪ ብስራት የሆነዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።