የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ አርብቶ አደሮችና ነዋሪዎች ገለፁ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 05/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ፥ ኢትዮጵያ ያቀደችውን ግዙፍ ልማት ጀምራ ማጠናቀቅ እንደምትችል ማሳያ ነው ሲሉ በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ አርብቶ አደሮችና ነዋሪዎች ገለፁ።
የግዱቡ ውሃ ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ገደብ በመካሄዱ ደስተኞች መሆናቸውን ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዛሬ መንግስት የግድቡ የመጨረሻና አራተኛ ዙር ሙሌቱን ይፋ ማድረጉን በተለያየ መንገድ መስማታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
እጅ ለእጅ ከተያያዘንና አንድነታችንን ካጠናከርን ገና በርካታ ትላልቅ ልማቶችን ጀምረን መጨረስ የምንችል ህዝቦች መሆናችንን ለዓለም እናስመሰክራለን ሲሉም ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የግድቡ ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚጠብቅብንን ድርሻ እንወጣለን፥ ሌላ ተጨማሪ ልማትም ጀምረን እንደ ህዳሴው ግድብ ሳናስተጓጉል እናጠናቅቃለን ሲሉም አቋማቸውን ገልፀዋል።
ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ቅርንጫፍ
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከ136 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ እንዲሻሻል ማስቻሉን አስታወቀ
በበዓላት ወቅት በሚፈጸሙ የእርድ ስነ-ስርዓት ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ