በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስር የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ዛሬ በይፋ ስራ ይጀምራሉ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስር የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ዛሬ በይፋ ስራ ይጀምራሉ

ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስር የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ዛሬ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

መቀመጫቸውን በስልጤ ዞን ያደረጉ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር ሴክተር መስሪያ ቤቶችም በተመሳሳይ ወደ ስራ ይገባሉ።

የማስጀመሪያ ሰነ ስርዓትም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይጀምራል።

በማስጀመሪያ ሰነ ስርዓቱ ላይ ለመሳተፍ በርካታ እንግዶች ወደ ወራቤ እየገቡ ነው።

ወራቤም እንግዶቿን እየተቀበለች ነው።

ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ