ህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ በማጎልበት በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርት ጽህፈት ቤት ገለፀ

ህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ በማጎልበት በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርት ጽህፈት ቤት ገለፀ

በዞኑ የበጎነትን ቀንን ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ታራሚዎች የተለያዩ ድጋፎችን ተደርጓል።

የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

በተለይም በመገባደድ ላይ ባላው የ2015 በጀት ዓመት በዞኑ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውንና በዚህም የተሻሉ ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለፁት አቶ ክብሩ በዛሬው ዕለትም የበጎነትን ቀንን ምክንያት በማድረግ ከንግግር ባለፈ ድጋፍ ለሚሹ የህግ ታራሚዎች በአካል በመቅረብ የተለያዩ ድገፎችን መደረጉን ተናግረዋል።

በጎነት ለዞኑ ማህበረሰብና ለአመራሩ አዲስ እንዳልሆነ የገለፁት ሃላፊው በቀጣይም መሠል ሥራዎች በተለያዩ ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚከናወኑም አስታውቀዋል።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የወጣቶች ዘሪፍ ሀላፊ አቶ አብዱ ድንቁ የዛሬው ዕለት የበጎነት በመሆኑ የተለያዩ ድጋፍች መደረጉን አንስተው በዞኑ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ በክረምትና በበጋ ወራት ላይ በርካታ የበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

አክለውም በዞኑ ድጋፍ ከሚሹ አካላት መካከል የህግ ታራሚዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ በዚህም የተለያዩ አልባሳት፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችና ለበዓል የሚሆኑ የበግ ስጦታዎችን ማበርከታቸውን አመላክተዋል።

በተላይም ያሉበትን ሁኔታ በመረዳት በየዓመቱ የዞኑ ማህበረሰብና ሌሎች አካላትን በማሳተፍ ጠያቂ ያጡ ታራሚዎች ይበልጥ ተጠቀሚ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነም ገልፀዋል።

በተደረገው ድጋፍ ላይ የዞኑ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴዎች አንድ ላይ በመሆን ኩፖን በመሸጥና በሌሎችም ተግባራት ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስገናቸውን አቅርበው ድጋፉ በቀጣይም ሊጠናከር እንደሚገባ አቶ አብዱ አስገንዝበዋል።

ኢንስፔክተር ሚስባሃ ግራኝ የወልቂጤ የማረሚያ ተቋም ስራ ስጋጅ ሲሆኑ በተቋሙ ከማረምና ከማነፅ ባለፈ የተለያዩ ሙያ ዓይነቶች እንዲቀስሙ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

በመሆኑም በዘሬው እለት የዞኑ መንግስት ታራሚዎች ያሉበትን ሁኔታ በመረዳት የተለያዩ ድጋፎች በመደረጉ በማመስገን በቀጣይም የማረሚያ ተቋማትን የሚደረጉ ድጋፍች መጠናከር አንዳለበት ገልፀዋል።

አንደንድ ያነጋገርናቸው ድጋፍ የተደረገላቸው ታራሚዎች በሰጡት አስትየያትም የበጎነትን ቀን መነሻ በማድረግ በተደረገው ድጋፍ እጅግ መደሰታቸውን ተናግረው ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ፡ ደጋጋ ሂሳቦ – ከወልቂጤ ጣቢያችን