የዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ ቤአ በዓል በታርጫ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ ቤአ በዓል በደማቅ ሁኔታ በታርጫ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ከየወረዳዎች የመጡ የባህል ቡድኖችም የብሔረሰቡን ባህልና ታርክ የሚዳስሱ የተለያዩ ትርዒቶችን እያሳዩም ይገኛሉ፡፡
በበዓሉ ስነ-ሥርዐት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ዕርሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ወገሾን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች እንድሁም የዳውሮ ብሄረሰብ ተወላጆችና ሌሎችም እንግዶች አየታደሙ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከ136 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ እንዲሻሻል ማስቻሉን አስታወቀ
በበዓላት ወቅት በሚፈጸሙ የእርድ ስነ-ስርዓት ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ