መስዕዋት ለሆኑ ጀግኖቻችን አድናቆት እየቸርን ለመጪው ትውልድ  የምትሆን ታላቅ ሀገር እናስረክባለን- አቶ አብርሃም መጫ

መስዕዋት ለሆኑ ጀግኖቻችን አድናቆት እየቸርን ለመጪው ትውልድ  የምትሆን ታላቅ ሀገር እናስረክባለን- አቶ አብርሃም መጫ

ሀዋሳ: ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ)  መስዕዋት ለሆኑ ጀግኖቻችን አድናቆት እየቸርን ለመጪው ትውልድ  የምትሆን ታላቅ ሀገር እናስረክባለን ሲሉ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሀም መጫ ተናገሩ፡፡

የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ አደባባይ በተከበረው የመስዋዕትነት ቀን ላይ የተገኙት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሀም መጫ  ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ያጋጠማትን ፈተናዎች በጀግኖች ልጆቿ መስዕዋትነት ከሙሉ ክብሯ ጋር ለዛሬ ቀን አብቅተዋታልና ምስጋና ይገብቸዋል ብለዋል፡፡

ቀኑ የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት አስበን የምንውልበት እና በኛ ትውልድም ሀገራችን ከኛ የምትፈልገውን መስዋዕትነት ለመክፈል እና ታሪክ ለማኖር የምንዘጋጅበት ነው ሲሉም  አክለዋል፡፡

ላለፉት ድንቅ ጀግኖች አድናቆትን እየቸርን ለመጪው ትውልድ  የምትሆን ታላቅ ሀገርም እናስረክባለን ነው ያሉት አቶ አብርሀም፡፡

መስዋዕትነት ዳር ድንበርን ከማስጠበቅ ባለፈ ከውስጥና ከውጭ ሀገርን የሚፈትን አደጋ በጋራ በመከላከል ጀግንነትን በተግባር ማሳየት እና ሀገርን በልማት ጎዳና ወደ ከፍታ መውሰድ በመሆኑ ይህን  መፈፀም ከኛ ይጠበቃል ብለዋል::

ዘጋቢ: ማሬ ቃጦ